አብርሆተ ዜና እና ማስታወቂያ
የአክሲዩን ዕጣ ሽያጭ ጊዜ መራዘም
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

አብርሆተ ስብእ የትምህርት ስልጠናና ንግድ አ/ማ
ኢትዮጵያዊነት በእምነት እውነትን (ፈሪሐ እግዚአብሔርን) መላበስ ፤ የምድር ዋና ሀብቷ ሰው እንደሆነ ማመን ፤ አእምሯዊ ጸጋን መጠቀም፤ ጥበብን መመርኮዝ ፤ የፊደል ገበታን በሆሄ ተርታ ሠርቶ ጸጋን መግለጫ ቀመር መፈልሰፍ ፤ የተፈጥሮ ሀብትን ማጤን ፤ የዓለሙን አሰላለፍ መተንተን ፤ የኑሮ ብልሃትን መዘየድ ፤ መደማመጥ መከባበርና መጠባበቅ ፤ ከቀደምት ቅርሶች (ታሪክ፣ባህል፣ወግ) በመማርና እውቀትን ገንዘብ በማድረግ ወደ ፊት መፈንጠር ነበር፡፡
ጥያቄው! ያ ምጡቅነት፣ ገናናነት፣ ኃያልነትና ግብረ ገብነት የት ተነነ? የት በነነ? የትስ ተዳፈነ?
በቁም ከተኛንበት ተቀሳቅሰን ከዚያ ከፊታችን ለመዋሐድ ምን አለን? በአለን ምን እንሠራለን? የሚል መፈንጠርያ መላምት የሚፈተንባቸው ስድስት መንደሮችን እነሆ ወጠንን::
ፍልስፍና
“አፍርቶ፣ አምርቶ፣ አባዝቶ፣ አሰራጭቶ፣ ሞልቶና አትረፍርፎ” በልህቀትና በልግስና ለመኖር መንገዱ ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን በግዕው ማዋሐድ ነው፡፡

ተልእኮ
የተቆለፈውን በር እየከፈተ ፥ የተደበቀውን ምሥጢር እየገለጠ ፥ የራቀውንም ሲሳይ እያቀረበ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ወደ ሆነ የባለጸግነት እልፍኝ የሚቀዝፍ ጠንካራ ኅብረት መገንባት::

ርእይ
በባለጠጋዋ ምድር ቅድስት ኢትዮጵያ ምጡቅ፣ ባለጠጋ፣ ገናና፣ ኃያልና የታፈረ ግብረ ገብ ትውልድ ማየት!!

መርኃ ጽድቅ
- የእራስን የኅሊና አተያይ ማስተካከል፣
- ሕልምን ከድል በግብር ማደላደል፣
- እስከ መትረፍ መኖር፡፡

እሴቶች
- ለውጥ[መንቃት፣መብቃት፣መፍታታት]
- ብልህነት [ፍልስፍና-ግኝት-ጥበብ]
- መሪነት [ሐሳብ-ካርታ-ሠራዊት]
- ኅብረት [ቅመራ-ለመዳ-ድል]
- ባህል [ሥራ-ጠጋ-ልግስና]

ግቦች
የሚከተሉትን መንደሮች መገንባት፡-
- ሕይወት ቀያሪ የትምህርት መንደር መገንባት፣
- የሕፃናት መዝናኛ መንደር መገንባት፣
- የቅመራ፣ ፍተናና ፈጠራ የተግባረ እድ ሥልጠና መንደር መገንባት፣
- የአልባሳት ዲዛይን፣ማምረቻና ማከፋፈያ መንደር መገንባት፣
- የግብርና ሥራ ማዘመኛና ማቀነባበሪያ መንደር መገንባት፣
- ፈጠራን ማስተዋወቂያና የገበያ ትስስር መንደር መገንባት፡፡
የጊዜ ሠሌዳ
ከጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም – መጋቢት 30/2014 ዓ.ም