ቀን፡ ግንቦት 28/2014 ዓ.ም
የባለ አክሲዩኖች አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
ጤና ይስጥልን የተከበራችሁ የአብርሆተ ሰብእ የት/ት ሥልጠናና ንግድ አ.ማ ባለ አክሲዮኖች!!
አክሲዩኑ በጀመራቸውና ቀጣይ ሥራዎቹ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ የባለ አክሲዩኖች አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የአክሲዩኑ አባላት ሰኔ 5/ 2014 ዓ.ም ፣እሑድ ልክ ከጧቱ 2፡30 ሰዓት በባሕር ዳር ከተማ፣ኖክ መስመር፣በሳፋሪ ሞል መሰብሰቢያ አዳራሽ
በሰዓቱ በግንባር/ በሕጋዊ ወኪል እንዲገኙልን በአክብሮት ጠርተነዎታል፡፡
አጀንዳዎች፡–
1. የአክሲዮኑን የሥራ እንቅስቃሴ ምልከታ
2. አዳዲስ ባለአክሲኖችን መቀበል
3. የተቋማት ግዢ
4. ዕጣን በተመለከተ
- በአክሲዩኑ በኩል የሚሸጥ ተጨማሪ ዕጣ ማፅደቅ
- የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጣን የማፅደቅ ሥልጣን መስጠት
- ባለአክሲዩን መተካት
5. የተቋም ምረቃ
የዳይሬክተሮች ቦርድ