የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ
ጤና ይስጥልን የተከበራችሁ የአብርሆተ ሰብእ የት/ት ሥልጠናና ንግድ አ.ማ ባለ አክሲዮኖች!!
አክሲዩኑ በቀጣይ ሥራዎቹ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የአክሲዩኑ አባላት ሐምሌ 11/ 2013 ዓ.ም ፣እሑድ ልክ ከጧቱ 2፡30 ሰዓት በባሕር ዳር ከተማ፣ከቅዱስ ጊዩርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ ፖሊ መስመር፣ ከአልማ ቢሮ ፊት ለፊት በሚገኘው በሰመር ላንድ ሆቴል አዳራሽ በሰዓቱ በግንባር/ በሕጋዊ ወኪል እንዲገኙልን በአክብሮት ጠርተነዎታል፡፡
አጀንዳዎች፡-
- የአክሲዮኑን የምስረታ ሂደት የሥራ ክንውን
- የአክሲዮኑን የመመስረቻና የመተዳደሪያ ደንብ ማፅደቅ/ የዳይሬክተሮች ቦርድና ሥራ አመራር መምረጥ
- የአክሲዮኑ ካፒታልና የእያንዳንዱ አባል የዕጣ መጠን
- በአክሲዩኑ በኩል የሚሸጥ ተጨማሪ ዕጣ ማፅደቅ
- ለ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት ሥራዎችንና በጀት ማፅደቅ
- የውጭ ኦዲተርን በተመለከተ
ማሳሰቢያ፡-
- መታወቂያ ይያዙ
- በሕጋዊ ወኪል የምትቀርቡ የውክልናውን ዋናና ኮፒ
- ስብሰባው ለማካሄድ ምልአተ ጉባዔ ያስፈልገዋል