ተልእኮ
የተቆለፈውን በር እየከፈተ ፥ የተደበቀውን ምሥጢር እየገለጠ ፥ የራቀውንም ሲሳይ እያቀረበ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ወደ ሆነ የባለጸግነት እልፍኝ የሚቀዝፍ ጠንካራ ኅብረት መገንባት::
ርእይ
በባለጠጋዋ ምድር ቅድስት ኢትዮጵያ ምጡቅ፣ ባለጠጋ፣ ገናና፣ ኃያልና የታፈረ ግብረ ገብ ትውልድ ማየት!!
መርኃ ጽድቅ
የእራስን የኅሊና አተያይ ማስተካከል፣ ሕልምን ከድል በግብር ማደላደል፣ እስከ መትረፍ መኖር፡፡
አብርሆተ ሰብእ የትምህርት ስልጠናና ንግድ አ/ማ
ኢትዮጵያዊነት በእምነት እውነትን (ፈሪሐ እግዚአብሔርን) መላበስ ፤ የምድር ዋና ሀብቷ ሰው እንደሆነ ማመን ፤ አእምሯዊ ጸጋን መጠቀም፤ ጥበብን መመርኮዝ ፤ የፊደል ገበታን በሆሄ ተርታ ሠርቶ ጸጋን መግለጫ ቀመር መፈልሰፍ ፤ የተፈጥሮ ሀብትን ማጤን ፤ የዓለሙን አሰላለፍ መተንተን ፤ የኑሮ ብልሃትን መዘየድ ፤ መደማመጥ መከባበርና መጠባበቅ ፤ ከቀደምት ቅርሶች (ታሪክ፣ባህል፣ወግ) በመማርና እውቀትን ገንዘብ በማድረግ ወደ ፊት መፈንጠር ነበር፡፡
ጥያቄው! ያ ምጡቅነት፣ ገናናነት፣ ኃያልነትና ግብረ ገብነት የት ተነነ? የት በነነ? የትስ ተዳፈነ?
በቁም ከተኛንበት ተቀሳቅሰን ከዚያ ከፊታችን ለመዋሐድ ምን አለን? በአለን ምን እንሠራለን? የሚል መፈንጠርያ መላምት የሚፈተንባቸው ስድስት መንደሮችን እነሆ ወጠንን::
ፍልስፍና
“አፍርቶ፣ አምርቶ፣ አባዝቶ፣ አሰራጭቶ፣ ሞልቶና አትረፍርፎ” በልህቀትና በልግስና ለመኖር መንገዱ ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን በግዕው ማዋሐድ ነው፡፡
እሴቶች
- ለውጥ[መንቃት፣መብቃት፣መፍታታት]
- ብልህነት [ፍልስፍና-ግኝት-ጥበብ]
- መሪነት [ሐሳብ-ካርታ-ሠራዊት]
- ኅብረት [ቅመራ-ለመዳ-ድል]
- ባህል [ሥራ-ጠጋ-ልግስና]
ግቦች
የሚከተሉትን መንደሮች መገንባት፡-
ሀ. የትምህርት መንደር
ለ. የሆቴልና መዝናኛ መንደር
ሐ. የአልባሳት ዲዛይን፣ማምረቻና ማከፋፈያ መንደር
መ. የግብርና ሥራ ማዘመኛና ማቀነባበርያ መንደር
ሠ. የተግባረ እድ ቅመራና ፈጠራ መንደር
ረ. ፈጠራን ማስተዋወቂያና የገበያ ትስስር መንደር
የጊዜ ሠሌዳ
ከጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም – ነሐሴ 30/2014 ዓ.ም
አሁናዊ ሁኔታ
- ከ600 በላይ ባለ አክሲዮኖች ፤ የንግድ ሥራ ላይ ያለ
የዕጣ ሽያጭ
- መግዛት የሚቻለው፡- ከ50 ዕጣዎች (50,000 ብር) ጀምሮ እስከ 1,000 ዕጣዎች (1,000,000 ብር)
- ሥራ ማስኬጃ ክፍያ፡- የዕጣውን 10%
የባንክ ሒሳብ ቋት ቁጥሮች
ተ/ቁ | ባንክ | የካፒታል | የአገልግሎት ክፍያ |
---|---|---|---|
1 | ዓባይ ባንክ | 261 111 688 755 4014 | 261 111 688 757 2027 |
2 | አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ | 301 661 | 300 400 |
3 | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 1 000 423 693 774 | 1 000 423 693 855 |
4 | አቢሲንያ ባንክ | 81 06 14 59 | 81 06 27 81 |
5 | አዋሽ ባንክ | 013 206 038 540 00 | 013 206 038 540 01 |
6 | ዳሽን ባንክ | 529 427 940 9011 | 529 427 940 7011 |
7 | አማራ ባንክ | 9 90 00 00 46 11 92 | 9 90 00 00 46 20 48 |
8 | ቡና ባንክ | 1349 52 8000 450 | 1349 52 8000 449 |
አክሲዮን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ነገሮች
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ (ዋናውና ኮፒ)
- ባንክ የከፈሉበት ደረሰኝ
- ሁለት 3 X 4 ጉርድ ፎቶ
- በልጆች ስም ለመግዛት የልጆች የልደት ካርድ፣ የአባት/እናት/ወይም የአሳዳጊ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ
- በድርጅት ስም አክሲዮን ለመግዛት
5.1. የድርጅቱ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
5.2. አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችል በሕጋዊ አካል የተሰጠ ውክልና
5.3. ማኅበራትና እድሮች የተመሰረቱበት መረጃ
- በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት
6.1. ፓስፖርታቸው የኢትዮጵያ ከሆነ የታደሰ ፓሥፖርት/መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ
6.2. የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን የታደሰ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ(ቢጫ ካርድ)